|

ለቀጣይ ትውልድ
ብሩህ ተስፋን እንገንባ

የተማሪዎች ቡድን
በአዲሱ ቤተ-መጻሕፍት ውስጥ
ክፍል ውስጥ ትምህርት

የትምህርት ቤታችን አጭር ታሪክ

የኮን አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ወረዳ የሚገኝ ትምህርት ቤት ነው። ትምህርት ቤቱ በ 1945 አ.ም ተቋቋሞ እስከ አሁን ድረስ ተማሪዎችን እየተቀበለ ለትልቅ ደረጃ ሲያደረስ የቆየ እድሜ ጠገብ አንጋፋ ትምህርት ቤት ነው።

ላለፉት 73 አመታት በቁጥር ይህ ነው ተብሎ ሊጠቀስ የማይችል በትምህርታቸው ሃገራቸውንና ወገኖቻቸውን የረዱና እየረዱ ያሉ ታላላቅ ሰዎችን ማፍራት የቻለ በክልሉ ከሚጠቀሱ ዝነኛ ትምህርት ቤቶች አንዱ ነው። ይህን ትምህርት ቤት ከሌሎች መሰል ትምህርት ቤቶች ለየት የሚያደርገው ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ከተለያዩ ወረዳዎች እንዲሁም በወረዳው ውስጥ ካሉ ከ25 የሚበልጡ ቀበሌዎች የሚመጡ ተማሪዎችን እየተቀበለ ያስተማረና እያስተማረ የሚገኝ መሆኑ ነው።

ተማሪዎች ክፍል ውስጥ

ፋውንዴሽናችን እንዴት ተጀመረ

ትምህርት ቤቱ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ማለትም የትምህርት ፋሲሊቲዎች (ግብአት) በበቂ ሁኔታ አለመኖር እና በቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርት አለመሰጠት ተማሪዎች ከሌሎች ትምህርት ቤት ተማሪዎች ጋር ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ እንቅፋት ሆኖ ቆይተዋል። ስለዚህ እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች በመገንዘብ የኮን ሃይስኩል ፋውንዴሽን ማቋቋም እንደ መፍትሔ ታቅዶ በትልቅ ራእይ የተጀመረ ፋውንዴሽን ነው። ስለሆነም ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር፣ በዚሁ ትምህርት ቤት ተምረው ትልቅ ደረጃ የደረሱ የቀድሞ ተማሪዎችን በመያዝ እንዲሁም ዓላማችን በመደገፍ ተባባሪ በመሆን የበኩላቸውን ኣሻራ ለማሳረፍ ፈቃደኛ በሆኑ ቅን ልቦና ባላቸው ግለሰቦችን ጭምር በማካተት የመፍትሔ አካል እንዲሆኑ አድርጎ ስራውን ጀምሯል።

ዋና ዋና የትኩረት መስኮች

በእነዚህ ቁልፍ መስኮች ላይ በማተኮር ዘላቂና አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት እንጥራለን።

የትምህርት ግብአቶች

የትምህርት ግብአቶችን አቅም በፈቀደ መጠን በማቅረብ የተማሪዎችን የመማር ሂደት እናግዛለን።

ዘመናዊ ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት

ተማሪዎችን ከዘመኑ የትምህርት ስርአት ጋር ጎን ለጎን እንዲሄዱ በዲጂታል የታገዘ የላይብረሪና ተጨማሪ ነፃ የኦንላይን ኮርሶችን እንዲያገኙ ማድረግ።

ለተማሪዎች ድጋፍ

የአቅም ውስንነት ያለባቸውን ተማሪዎችን በመደገፍ የትምህርት ህልማቸው እውን እንዲሆን ማድረግና መከታተል።

የትምህርት ቤቱን አስተዳደሮች ይተዋወቁ

ሀብተማርያም ልባሴ

ሀብተማርያም ልባሴ

ርእሰ መምህር

ማንኛውም ያደጉ ሀገራት የእድገት መሠረት ምክንያት ትምህርት እና የተማረ የሰው ሃይል ሲሆን የተማረ የሰው ሃይል ዋና ምንጭ ደግሞ የትምህርት ተቋማት ናቸው ። ስለዚህ ትምህርት ቤቶች የተሻለ የሰው ሐይል እንዲያፈሩ ከተፈለገ በቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርት እና ግብዓት መሟላት ተቀዳሚ ተግባር ነው ። ስለሆነም ይህ ፋውንዴሽን የተማሪዎችን እና የትምህርት ቤቱን የግብዓት ችግር አቅም በፈቀደ ቀስበቀስ እንደሚፈታ እና የተማሪዎች ውጤት ላይ ልዩነት እንደሚፈጥር ጽኑ እምነት አለኝ

የት/ቤቱ አጭር መረጃ

መረጃ እና የስራ ሰዓት
  • 🏫
    የት/ቤት ስምኮን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
  • 📞
    ስልክ፦+251 33 443 0058
  • ✉️
    ኢሜል፦--
የስራ ሰዓት፦

ሰኞ - አርብ፦ ጠዋት 1:30 - 11:30 ከሰአት

ቅዳሜ - እሑድ፦ ዝግ ነው

የተጀመረውን እንቅስቃሴውን ይቀላቀሉ

የእርስዎ ድጋፍ በቀጥታ የተማሪዎችን ህይወት ይለውጣል። ምን ያህል እንደተጓዝን እና ግባችንን ለመምታት ምን ያህል እንደቀረን ይመልከቱ።( የገንዘብ ቻርት ላይ የሚታየው ቁጥር ከገንዘብ መስጫ በተጨማሪ በማቴርያል ድጋፍ የተገኘውን ዋጋ ወደ ገንዘብ በመቀየር የተጨመረ ሊሆን ይችላል። )

ብርተሰብስቧል
ግብ 1,000,000 ብርቀሪው: 1,000,000 ብር
0%25%50%75%100%

+

ተማሪዎች ተጠቃሚ ሆነዋል

ቤተ-መጻሕፍት ተደግፈዋል

+

ተማሪዎች የቁሳቁስ ድጋፍ

+

የትምህርት አይነቶች ተሸፍነዋል

ድጋፍ ያደረጉ ሰዎች

የምስራች

በዌብሳይታችን ያካተትናቸው ትልቅ ፍሬ የምንጠብቅባቸውን ገጽኦች እናስተዋውቃችሁ፡

ነፃ የኦንላይን ትምህርቶች

ዲጂታል ላይብራሪ

ቨርቹዋል ላብራቶሪ

በቅርብ የሚጀምር

ነፃ የኦንላይን ትምህርቶች

በአሁኑ ጊዜ ተመራጭ በሆኑና እንደ ሃርቫርድ ባሉ ታላላቅ በሚባሉ ዩኒቨርስቲዎች የሚሰጡ ማንኛውንም ነፃ የኦንላይን የትምህርት እድል እንድታገኙ ፋውንዴሽናችን አመቻችቷል።

የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ከፋውንዴሽናችን ጋር የተያያዙ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ዝግጅቶችን ይከታተሉ።

Kone High School Foundation" በሚል የተቋቋመው የበጎ አድራጎት ድርጅት የትምህርት ቁሳቁስ ማሟላት ለአልቻሉ ተማሪዎች ድጋፍ አደረገ።

Sep 23, 2025

Kone High School Foundation" በሚል የተቋቋመው የበጎ አድራጎት ድርጅት የትምህርት ቁሳቁስ ማሟላት ለአልቻሉ ተማሪዎች ድጋፍ አደረገ።

ኮን፦ መስከረም 13/2018 ዓ.ም (ዋድላ ኮሙዩኒኬሽን)በሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ "Kone High School Foundation" በሚል የተቋቋመው የበጎ አድራጎት ድርጅት የትምህርት ቁሳቁስ ማሟላት ለአልቻሉ 50 የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች 50 ደርዘን ደብተርና 2 ባኮ ስክርቢቶ በዛሬው ዕለት ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉ የተደረገው የቀድሞ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎችና የወረዳው ተወላጆች በነበሩት የፋውንዴሽኑ መስራቾች እንደሆነ ተመላክቷል።

በፌስቡክ ላይ ያንብቡ
በሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ ለኮን 2ኛና መሰናዶ ትምህርት ቤት ከ65ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ መጽሀፍት ድጋፍ ተደረገ።

June 15, 2025

በሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ ለኮን 2ኛና መሰናዶ ትምህርት ቤት ከ65ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ መጽሀፍት ድጋፍ ተደረገ።

ድጋፉ የተደረገው የቀድሞ የትምህርት ቤቱ ተማሪና መምህር በነበሩት በአቶ ሰለሞን ይመር ነዋሪነታቸው በአሜሪካን ሀገር ሲሆን በዛሬው ዕለት ለኮን 2ኛና መሰናዶ ትምህርት ቤት 1መቶ 34 መጽሀፍት ከ65ሺህ ብር በላይ ወጭ በማድረግ ገዝተው በቀድሞ ጓደኛቸውና በትምህርት ቤቱ መምህር አቤል ቢሰጠኝ በኩል በሚመለከታቸው አካላት አማካኝነት ርክክብ ተደርጓል።

በፌስቡክ ላይ ያንብቡ

ለውጡን ዛሬውኑ ይቀላቀሉ!

የእርስዎ ተሳትፎ፣ በየትኛውም መልኩ ቢሆን፣ ትልቅ ለውጥ ያመጣል። የኮን ሃይስኩል ተማሪዎችን ህልም እውን ለማድረግ አብረን እንስራ።